ማስታወቂያ       

የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በሳይንሳዊ ዕውቀትና በፈጠራ ክህሎት ሀገራችንን ወደ ሁለንተናዊ ብልፅግና የሚያሸጋግር ድልድይ የመገንባትን ራዕይ ሰንቆ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ ይህን ራዕይ ለማሳካት ከሚያከናውናቸው ተግባራት አንዱ የምርምር ስራዎችን መደገፍ ነው፡፡ በመሆኑም በግብርና፣ በጤና፣ በማኑፋክቸሪንግና ኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዘርፎች በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ ለመመረቂያ የተሰሩ የምርምር ስራዎችን በየሩብ ዓመቱ ከደጋፊ አካላት ጋር በሚካሄዱ የዉይይት መድረኮች እንዲቀርቡ በማድረግ የድጋፍ ስራ ይሰራል፡፡ ስለሆነም ከላይ በተጠቀሱት ዘርፎች የተሰሩ የምርምር ስራዎች ያላችሁ እሰከ መስከረም 20/2010 ዓ.ም ድረስ ከታች በተገለፀው አድራሻ በመላክ በመድረኩ ላይ እንድትሳተፉ ተጋብዛችኋል፡፡

                     

  • ኢሜይል scienceaward2007@gmail.com
  • ስልክ 0966798651/ 0910300502
  • በአካል ማመልከት ለምትፈልጉ ሊሴ ገብረማርያም ት/ቤት ጀርባ በሚገኘው ዋናው መስሪያ ቤት 2ኛ ፎቅ ሽልማትና ገበያ ልማት ዳይሬክቶሬት ቢሮ በመቅረብ ማመልከት ትችላላችሁ፡፡

          አመልካቾች ማሟላት የሚገባቸው

  1. ከተመረቁበት ተቋም የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ 
  2. ያዘጋጁት የመመረቂያ ፅሁፍ ሙሉ ፕሮፖዛል
  3. HR

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር