Skip to Content

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፕሬዝደንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን ጎበኙ።

Ministry of Science and Technology successfully launched the first Ethiopian drone.

ከ35 በላይ የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ አንድ መቶ ወጣት ሴቶች የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን ጎብኝተዋል።

Ministry of science and technology signed Five Years Agreement with International Atomic Energy Agency.

ኢትዮጲያ ከህክምና መሳርያዎች ተጠቃሚነት ወደ አምራችነት ለመሸጋገር እየሰራች ነው ተባለ፡፡

Back

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በአዲስ አበባ ከተማ ያስገነባቸውን የሳይንስ ካፌዎች አስመረቀ፡፡

የሳይንስ ካፌዎቹ የሳይንስና ቴክኖሎጂን ባህል፣ ግንዛቤ እና አስተሳሰብ በህብረተሰቡ ውስጥ እንዲያድግ እና ወጣቶች የቴክኖሎጂ እውቀትን በመቅሰም ቴክኖሎጂን መሰረት ያደረገ ስራ ፈጣሪ እንዲሆኑ የሚያስችል ነው፡፡

የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ጋር በመተባባር ያስገነባቸውን እነዚህን ካፌዎች የኢ... ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ተገኝተው መርቀዋል፡፡

የሳይንስ ካፌዎቹ የቤተ መፀሐፍት አገልግሎት፣ በዲጂታል እና በእትም የተዘጋጁ ሳይንሳዊ መረጃዎችን የያዙ መፅሃፍት፣ በሳይንሳዊ ጉዳዮች ዙሪያ እየተወያዩ አገልግሎት የሚያገኙበት ካፍቴሪያ፣ ነፃ የኢንትርኔት አገልግሎቶችን፣ የፈጠራ ባለሙያዎች የፈጠራ ስራ ውጤቶቻቸውን የሚያቀርቡት ቦታ የያዘ ነው፡፡

ከህዳር 4/2010 እስከ ህዳር 8/2010 የሚከበረውን 3ኛውን የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን አውደ ርዕይ ሳምንትንም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የከፈቱ ሲሆን ለወጣቶች፣ ለተመራማሪዎች እና ለቴክኖሎጂ ባለሙያዎች እና ለሌሎችም ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡

በአውደ ርዕዩ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተጠሪ ተቋማት፣ የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲቲዩት፣ የኢትዮጵያ ግብርና ኢንስቲቲዩት፣ አይኮግ ላብ እና ሌሎችም ስራዎቻቸውን አቅርበዋል፡፡

በዚህ በ3ኛው የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን አውደ ርዕይ ሳምንት ለተከታታይ አራት ቀናት የሚቆይ የፓናል ውይይት እየተደረገ ሲሆን፤ በውይይቱም ባለፉት 7 አመታት በፈጠራና በምርምር ስራ እውቅናና ሽልማት ያገኙ ግለሰቦችና ተቋማት፤ ስራዎቻቸው ምን ፋይዳ አመጡ? መንግስትና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ምን ድጋፍ አደረጉላቸው? በጥቅሉ ስራዎቻቸው የት ደርሰዋል የሚለውን ለመለየት ያለመ ነው፡፡

በውይይቱም ሚኒስቴር መስሪያቤቱ ለነዚህ የፈጠራና  የምርምር ስራ ባለቤቶች የሚያደርገውን ድጋፍ በውይይቱ በሚሳተፉት የፈጠራና የምርምር ስራ ባለቤቶች ይገመገማል፡፡

የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ኢንጂ. ጌታሁን መኩሪያ እንዳሉ  በሀገራችን ያሉትን ሳይንቲስቶች፣ ኢንጂነሮች፣ ተመራማሪዎች፣ ኢንዳስትሪያሊስቶች ወዘተ ተጠቅመን የሀገራችን ኢኮኖሚ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ውጤቶችን በመደገፍ በምንችላው አቅም ማሳደግ ይጠበቅብናል ፡፡

8ኛዉ ብሄራዊ የሳይንስ፣ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን የእውቅናና የሽልማት ስነ-ስርዓት፤ ህዳር 9/2010 ዓ.ም በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ አዳራሽ ይክናወናል፡፡ በእለቱም በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አቅራቢነት በምርምር እና በፈጠራ ስራ 144 ግለሰቦች እና ለአንድ ድርጅት በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ሽልማትና እውቅና ይሰጣቸዋል፡፡


Message from the Minister Message from the Minister

Message from the Minister

H.E. Dr.-Ing. Getahun Mekuria Kuma has been appointed as the new Minister for Science and Technology beginning the 1st of November 2016. The appointment is part of Prime Minister Hailemariam Desalegn's cabinet reshuffle that came in the first week of November.

H.E. Dr.-Ing. Getahun has served the Ministry for the past two years as State Minister and Director General. Previously, H.E. Dr.-Ing. Getahun worked for the Addis Ababa Institute of Technology of Addis Ababa University in different academic and management capacities. He earned his BSc and MSc degrees in Electrical Engineering from Addis Ababa University. He completed his PhD degree in the same field at the University of Duisburg-Essen, Germany. The appointment of H.E. Dr.-Ing. Getahun as the Minister for Science and Technology is expected to galvanize the transformation process that the Ministry has already embarked on.

 

ፈጥነዉ የሚደርሱና ድርቅን መቋቋም የሚችሉ የማሽላ ዝሪያዎችን ማፍለቅ

ማሽላ በአገራችን ለምግብነት ከሚሰጠው አገልገሎት በተጨማሪ ለእንስሳ መኖነት እና ለማገዶ በሚሰጠው አገለልግሎት ይታወቃል፡፡ በአብዛኛው ዝናብ አጠር በሆኑ ቆላማ ቦታዎች የሚበቅል ሲሆን ሀገር በቀል ሰብል ከመሆኑ የተነሳ አርሶ አደሩ ባህላዊ የአመራረት ዘዴዎችን በስፋት በመጠቀም ያመርታል፡፡

በመረጣ የዝርያ ማሻሻል ዘዴ ሀገር በቀል ዶሮ ምርታማነት ማሻሻልና ለአነስተኛ አርቢዎች ተስማሚነት ጥናት

የዝርያው ምርታማነትና ለሀገራችን ተስማሚነቱ ለ2 ዓመታት ቁጥራቸው 4,700 በላይ የሆኑ ዶሮዎች ላይ በደብረ ዘይት ምርምር ማዕከል የተፈተሸና ውጤቱ ከታየ በኋላ ለአርቢዎች ተሰራጭቷል ለአብነትም፡-

ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ለኢኮኖሚ እድገት

ሀገራት ነባራዊ ሁኔታቸውንና ስነ-ምህዳራዊ ባህሪውን አጥንተው ተስማሚ እና ውጤታማ ቴክኖሎጂዎች ላይ ትኩረት በማድረግ መስራታቸው አለም በምትፈጥንበት እሩጫ ተሳታፊ እንዲሆኑ ያስችላቸዋል፡፡

የተሸላሚዎች ስራ

ከምርምርና የፈጠራ አካላት ጋር በጋራ መስራት የምትፈልጉ ወይም የምርምር/የፈጠራ ውጤቶቹ ተጠቃሚ መሆን የምትፈልጉ ከታች በተገለፁት አድራሻዎች በመጠቀም ማግኘት ትችሉ ዘንድ የፈጠራዎቹና የምርምሩ አጭር መግለጫ ከታች እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

Weekly Visitor Status Weekly Visitor Status

// ]]>