Skip to Content

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፕሬዝደንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን ጎበኙ።

Ministry of Science and Technology successfully launched the first Ethiopian drone.

ከ35 በላይ የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ አንድ መቶ ወጣት ሴቶች የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን ጎብኝተዋል።

Ministry of science and technology signed Five Years Agreement with International Atomic Energy Agency.

ኢትዮጲያ ከህክምና መሳርያዎች ተጠቃሚነት ወደ አምራችነት ለመሸጋገር እየሰራች ነው ተባለ፡፡

Back

የዘላቂ ልማት ግቦችን ስኬት ለማረጋገጥ የሰው እና የባዮስፌር ጥበቃ ስራ አካሄድ የተመጣጠነ እና በሳይንሳዊ ምርምር የተደገፈ መሆን አለበት፡፡

የዘላቂ ልማት ግቦችን ስኬት ለማረጋገጥ የሰው እና የባዮስፌር ጥበቃ ስራ አካሄድ የተመጣጠነ መሆን እና በሳይንሳዊ ምርምር የተደገፈ መሆን አለበት፡፡ የብሄራዊ የሰዉ እና የባዮስፌር ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባዉን በአዝመን ሆቴል አካሂዷል፡፡ የመሬት መራቆት፣ የአፈ ርጨዋማነት፣ የውሃ እጥረት፣ የበሽታዎች መስፋፋት እና በሽታዉን ለመከላከል የምንጠቀምበት መድሃኒት ችግር ማስከተል፣ በሃይቆች ላይ እየተደቀነ ያለው የእንቦጭ አረም፣ ለታዳሽ ሃይል ትኩረት ያለመስጠት እና የመሳሰሉት በባዮስፌሩ ላይ የተደቀኑ አደጋዎች መሆናቸው በስብሰባዉ ላይ ተነግሯል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ለችግሮች በጋራ የመስራት ልምድ አለማዳበርና ለችግሮች ፈጣን ምላሽ ከመስጠት አንፃር የሚታዩ ችግሮች እንዳሉም ተጠቅሷል፡፡ በጣና ሃይቅ ላይ የተደቀነዉን የእምቦጭ አረም በመከላከል በኩል የታዩ መዘግየቶች ለማሳያነት ተነስቷል፡፡ ባዮስፌሩን በመጠበቅ አና አካባቢን ለኑሮ ምቹ በማድረግ እንዲሁም የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ ምርታማ የሆኑ ዜጎችን ማፍራት ይገባልም ነዉ የተባለዉ፡፡ በመደበኛ ስብሰባዉ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተጠሪ ተቋማት፣ የተለያዩ ዪኒቨረሲቲ ተወካዮች፣ ከክልል እና ከዞን የተውጣጡ የአካባቢ ጥበቃ ባለሙያዎች፣ ከክልል መንግስታት፣ ከሙያ ማህበራት፣ ከኢትዮጵያ የዱር እንሰሳት ጥበቃ ኢንስቲቲዩት፣ ጂ አይ ዜድ (Giz)፣ ዩኒክናቡ (UNIQUE NABU) እና ከሚመለከታቸዉ መስሪያ ቤቶች የተዉጣጡ የኮሚቴዉ አባላት ታድመዉበታል፡፡ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር አፍወርቅ ካሱ እንዳሉት የዬኔስኮ የባዮስፌር ጥበቃ ፕሮግራምን በኢትዮጵያ በመተግበር ለዘላቂ ልማት ግቦች ተግባራዊነት መስራት ይጠበቅብናል፡፡

የዘላቂ ልማት ግቦችን ስኬት ለማረጋገጥ የሰው እና የባዮስፌር ጥበቃ ስራ አካሄድ የተመጣጠነ መሆን እና በሳይንሳዊ ምርምር የተደገፈ መሆን አለበት ያሉት የሳይንስና ቴክኒሎጂ ሚኒስቴር የሚኒስትሩ የቴክኖሎጂ አማካሪ አቶ አብዱረዛቅ ኡመር ናቸዉ፡፡ የደኖች መመንጠር እና የአፈር መሸርሸርን በመከላከል ስነ ህይወቱን መጠበቅ እንደሚገባም ተጠቁሟል፡፡ በአሁኑ ወቅት በሃይቆች ላይ እየተንሰራፋ የመጣዉ የእምቦጭ አረም ላይ የተወሰዱ እርምጃዎች መዘግየት ይታይባቸዋል የተባለ ሲሆን አረሙ ለታላቁ የህዳሴ ግድብ ስጋት የማይሆንበት ምንም ምክንያት የለም ያሉት ደግሞ በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ መምህር እና ተመራማሪ የሆኑት ዶክተር ሽመልስ አይናለም ናቸዉ፡፡


Message from the Minister Message from the Minister

Message from the Minister

H.E. Dr.-Ing. Getahun Mekuria Kuma has been appointed as the new Minister for Science and Technology beginning the 1st of November 2016. The appointment is part of Prime Minister Hailemariam Desalegn's cabinet reshuffle that came in the first week of November.

H.E. Dr.-Ing. Getahun has served the Ministry for the past two years as State Minister and Director General. Previously, H.E. Dr.-Ing. Getahun worked for the Addis Ababa Institute of Technology of Addis Ababa University in different academic and management capacities. He earned his BSc and MSc degrees in Electrical Engineering from Addis Ababa University. He completed his PhD degree in the same field at the University of Duisburg-Essen, Germany. The appointment of H.E. Dr.-Ing. Getahun as the Minister for Science and Technology is expected to galvanize the transformation process that the Ministry has already embarked on.

 

ፈጥነዉ የሚደርሱና ድርቅን መቋቋም የሚችሉ የማሽላ ዝሪያዎችን ማፍለቅ

ማሽላ በአገራችን ለምግብነት ከሚሰጠው አገልገሎት በተጨማሪ ለእንስሳ መኖነት እና ለማገዶ በሚሰጠው አገለልግሎት ይታወቃል፡፡ በአብዛኛው ዝናብ አጠር በሆኑ ቆላማ ቦታዎች የሚበቅል ሲሆን ሀገር በቀል ሰብል ከመሆኑ የተነሳ አርሶ አደሩ ባህላዊ የአመራረት ዘዴዎችን በስፋት በመጠቀም ያመርታል፡፡

በመረጣ የዝርያ ማሻሻል ዘዴ ሀገር በቀል ዶሮ ምርታማነት ማሻሻልና ለአነስተኛ አርቢዎች ተስማሚነት ጥናት

የዝርያው ምርታማነትና ለሀገራችን ተስማሚነቱ ለ2 ዓመታት ቁጥራቸው 4,700 በላይ የሆኑ ዶሮዎች ላይ በደብረ ዘይት ምርምር ማዕከል የተፈተሸና ውጤቱ ከታየ በኋላ ለአርቢዎች ተሰራጭቷል ለአብነትም፡-

ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ለኢኮኖሚ እድገት

ሀገራት ነባራዊ ሁኔታቸውንና ስነ-ምህዳራዊ ባህሪውን አጥንተው ተስማሚ እና ውጤታማ ቴክኖሎጂዎች ላይ ትኩረት በማድረግ መስራታቸው አለም በምትፈጥንበት እሩጫ ተሳታፊ እንዲሆኑ ያስችላቸዋል፡፡

የተሸላሚዎች ስራ

ከምርምርና የፈጠራ አካላት ጋር በጋራ መስራት የምትፈልጉ ወይም የምርምር/የፈጠራ ውጤቶቹ ተጠቃሚ መሆን የምትፈልጉ ከታች በተገለፁት አድራሻዎች በመጠቀም ማግኘት ትችሉ ዘንድ የፈጠራዎቹና የምርምሩ አጭር መግለጫ ከታች እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

Weekly Visitor Status Weekly Visitor Status

// ]]>