Skip to Content

The 8th National S.T.I Award

The 3rd STI-WEEK Science Cafe Opening

The 3rd STI-WEEK Exhibition

IAEA Director General Yukiya Amano met with H.E.Dr.ING Getahun Mekuria

H.E. Dr. Ing. Getahun Mekuria, FDRE Minister of Science and Technology with Professor Afework Kassu, Deputy Minister.

His Excellency Dr./Eng. Getahun Mekuriya, Minister of Science & Technology, invited Mr Solomon Mulugeta to recognized him as an ambassador of science and technology.

Latest Video Latest Video

Latest News Latest News

Latest News


በሳይንስናቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የሴቶችና ወጣቶች ዳይሬክቶሬት ለዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የገንዘብ ድጋፍ አደረገ፡፡

18/01/2018
የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የሴቶችና ወጣቶች ዳይሬክቶሬት ከተለያዩ የመንግስት ተቋማትና የግል ድርጅቶች ፈንድ በማፈላለግ በአዳማና በአዲስ አበባ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲዎች በኢኮኖሚ እጥረት ምክንያት ትምህርታቸውን ለመከታተል የተቸገሩ 92 የኢንጂነሪግ ተማሪዎች በየሶስት ወር ለየአንዳንዳቸው 1200 ብር ድጋፍ እያደረገ ይገኛል፡፡

በሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የጥራት ስራ አመራር ስርዓት ደረጃ (ISO 9001:2015 ) ትግበራ ሰነድ እየተዘጋጀ ነው፡፡

18/01/2018
የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የጥራት ስራ አመራር ስርዓት ደረጃን (ISO 9001:2015) ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል ሰነድ የብሔራዊ የጥራት መሰረተ ልማት ዳይሬክቶሬት ከሪፎርም ዳይሬክቶሬት ጋር በመተባበር በሚኒስትር መስሪያ ቤቱ በተቋቋመው ግብረ ሀይል በቢሾፍቱ ከተማ ከጥር 05- 8/2010 ዓ.ም እየተዘጋጀ ይገኛል ፡፡

በጋምቤላ ክልል የሚገኘው የማጃንግ ደን በዮኔስኮ የከባቢ ህይወት ጥበቃ /የባዮስፌር ሪዘርቭ/ አለም አቀፍ ትስስር ውስጥ ገብቶ ተመረቀ

01/01/2018
በምረቃ ስነ– ስርዓቱ ላይ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂ. ጌታሁን መኩሪያ፣ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ሚኒስትሩ ዶክተር ነገሪ ሌንጮ፣ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር ዶክተር ጋትሉዋክ ቱት እንዲሁም የፌደራል እና የክልል የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

የሳይንስ ካፌ በአማራ ክልል ሊገነባ ነው፡፡

12/01/2018
የኢ.ፊ.ዲ.ሪ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከአማራ ክልል የሳይንስ ቴክኖሎጂና ኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ኮሚሽን ጋር በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በተመረጡ ዋና ዋና ከተሞች አምስት የሳይንስ ካፌዎችን ለመገንባት የሚያስችል የስምምነት ሰነድ ተፈራርሟል፡፡

የጊዜ ብክነትን እንደ ሃብት ብክነት የመመልከት ባህል ሊለመድ ይገባል፡፡

09/01/2018
የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር የሙያ ማህበራት እና የባለድራሻ አካላትን የ6 ወር እቅድ አፈፃፀም ገምግሟል፡፡

Message from the Minister Message from the Minister

Message from the Minister

H.E. Dr.-Ing. Getahun Mekuria Kuma has been appointed as the new Minister for Science and Technology beginning the 1st of November 2016. The appointment is part of Prime Minister Hailemariam Desalegn's cabinet reshuffle that came in the first week of November.

H.E. Dr.-Ing. Getahun has served the Ministry for the past two years as State Minister and Director General. Previously, H.E. Dr.-Ing. Getahun worked for the Addis Ababa Institute of Technology of Addis Ababa University in different academic and management capacities. He earned his BSc and MSc degrees in Electrical Engineering from Addis Ababa University. He completed his PhD degree in the same field at the University of Duisburg-Essen, Germany. The appointment of H.E. Dr.-Ing. Getahun as the Minister for Science and Technology is expected to galvanize the transformation process that the Ministry has already embarked on.

 

Back

ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ለኢኮኖሚ እድገት

ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ለኢኮኖሚ እድገት 

    ሀገራት ነባራዊ ሁኔታቸውንና ስነ-ምህዳራዊ ባህሪውን አጥንተው ተስማሚ እና ውጤታማ ቴክኖሎጂዎች ላይ ትኩረት በማድረግ መስራታቸው አለም በምትፈጥንበት እሩጫ ተሳታፊ እንዲሆኑ ያስችላቸዋል፡፡ በተለይም ታዳጊ ሀገራት የአለም ሁኔታ ተረድተው ሀገራቸውን በአቋራጭ ወደ አንደኛው አለም ፈጣን እሩጫ መቀላቀል ግድ ይላቸዋል፡፡ እነዚህ በፈጣን እሩጫ እድገታቸውን የሚመሩ ሀገራት እየተጠቀሙበት ያለው አንዱ የቴክኖሎጂ ዘርፍ ኢመርጅግ ቴክኖሎጂ ሲሆን ምርትና ምርታማነት ለማሳድግ እንዲሁም የማህበረሰቡን ገቢና የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል ወሳኝ ነው፡፡

 ኢትዮጵያችን የጀመረችው የህዳሴ ጉዞ ለማፍጠን፤ የግብርና መር ኢኮኖሚ ወደ ኢንዱስትሪ መር ለመለወጥና አስተማማኝ ኢኮኖሚ ለመገንባት  የኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ዘርፎች ላይ ትኩረት አድርጎ መስራት ወሳኝ ጉዳይ ነው፡፡

   “ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ” አዲስ ወይም ነባር በሆኑ እና በተሻሻሉ እውቀት ላይ መሰረት የሚያደርጉ፣ በፈጣን ልማት ረገድ ከፍተኛ የሆነ የመወዳደሪያ አቅምን መገንባት የሚያስችሉ፣ በኢኮኖሚው፣ በማህበራዊው እና በፖለቲካዊው ምህዳር ተጨባጭና ዘላቂ እድገትን ማስመዝገብ የሚያስችሉ፣ ጠቀሜታቸው ዘርፈ-ብዙ የሆኑ፣ ተቀባይነታቸው እያደገ የመጣ እና በአለም አቀፍም ሆነ በሀገር ደረጃ ለተፈጠሩትና ለሚፈጠሩት ችግሮች መፍትሄ ለማስቀመጥ እድሉን የሚፈጥሩ ቴክኖሎጂዎች ማለት ነው፡፡

                 የተወሰኑትን በዝርዝር ለማየት ያህል

ባዮ ቴክኖሎጂ፡- ይህ ዘርፍ ህይወት ያላቸው አካላት ወይም ህዋስ ወይም ደግሞ በነሱ የሚመረቱ ቁሶች ዘመናዊ የቤተ ሙከራ ዘዴዎችን በመጠቀም የተለያዩ ኬሚካላዊ ሂደቶችን በማሻሻል ለሰው ልጅ ጠቃሚ የሆኑ የግብርና፣ የህክምና፣ የኢንዱስትሪና፣ የአካባቢ ጥበቃ ተግባራትን በማከናወን ዉጤት የማምጣት ሂደት ነው፡፡

ማቴሪያል ሳይንስ፡- ይህ የቴክኖሎጂ ዘርፍ በምድር ላይ የምንጠቀማቸው መገልገያዎች ( ቁስአካል) ባህሪ ላይ ጥናት የሚያደርግ ነው፡፡ ማለትም  በሀይል አጠቃቀም፣   በትራንስፖርት ዘርፍ፣ በማምረቻና ምርት ማሸጊያዎች፣ አየር ንብረትና ጥበቃ ወዘተ.. ኢኮኖሚን ከፍ የማድረግ አቅሙ የላቀ ነው፡፡

ናኖቴክኖሎጂ፡- የንጥረ ነገሮችን መል   አካላዊ፣ ኬሚካላዊ እና ባይሎጂካዊ ገፀ-ባህሪያትንና መዋቅሮች በአንድ ቢሊዮንኛ (1 ናኖ ሜትር) መለኪያ ደረጃ በማቀናበር መሰረታዊ የሆኑ አዳዲስ ምርቶችና መሳሪያዎችን የሚያስገኝና የሚተገብር ቴክኖሎጂ ነው፡፡

ምልስ ምህንድስና፡- አንድ ምርት ተመርቶ ለአገልግሎት ዝግጁ ከሆነ በኋላ ከእንደገና የተሰራበት ግብዓትና ሂደት፣ ጊዜ፣ ስፋት ቦታና ጥቅም አንፃር በማጥናት ካለው ነባራዊ ሁኔታ ጋር በማጣጣም መልሶ የማምረትና የመጠቀም ሂደት ወይም ቴክኖሎጂ ነው፡፡

አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ፡- የሰው ልጅ የእለት ተዕለት ተግባራችን በብቃት ለማከናወን የተለያዩ እውቀት ተኮር ስርዓቶችና የኮምፒዊተር ፕሮግራሞችን በማበልፀግና በመጫን የመሳሪያዎችን አገልግሎት ሰው ሰራሽ አስተውሎት በተላበሰ መልኩ እንዲተገብሩ የሚያስችል የቴክኖሎጂ ዘርፍ ነው፡፡  የመሳሪያ ሀይላት የሚፈጀው ጊዜና የቦታ ስፋት የምርቱ ሂደት ደረጃዎች በጠቅላላ እንዴት እንደሚሰራና ለምን አገልግሎት እንደሚውል በጥንቃቄ በማስተዋልና በማጥናት ካለው ነባራዊ ሁኔታ በመነሳት ተጠቃሚውን ባገናዘበ መልኩ መልሶ ወይም ደግሞ መሰራት /ማምረት  ማለት ነው፡፡ እነዚህ የቴክኖሎጂ ዘርፎች በሀገር እድገትና ግንባታ  በጣም የላቀ ጠቀሜታ ያላቸውና  ትልቅ ለውጥ መፍጠር የሚችሉ ናቸው፡፡ 

የቴክኖሎጂ አቅም ደረጃ የሀገራት የኢኮኖሚ አቅም ከፍታና ዝቅታ አስተማማኝነት ማሳያ እየሆነ ነው፡፡  ያደገ የቴክኖሎጂ አቅም አስተማማኝ ኢኮኖሚ መገንባት እና የሀገራት የመሪነት ሚናቸው ከፍ ማድረግ ያስችላል፡፡

ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂዎችን ለማልማት ፈጠራ፣ ምርምር፣ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፖሊሲ፣ የቴክኖሎጂ ውድድርና የማበረታቻ ስርዓት እና ሌሎች መንገዶች ጉልህ ሚና ይጫወታሉ፡፡ በዚህ መንገድ ቴክኖሎጂዎቹን በማበልፀግ  የስራ እድል፣ የተወዳዳሪነት መንፈስ፣ የገበያ መስፋፋት፣ ምርትና ምርታማነትን ማሳደግና ሌሎች ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎችን ማግኘት ይቻላል፡፡  ምንም እንኳ ቴክኖሎጂዎቹ ያላቸው ፋይዳ እጅጉን የጎላ ቢሆንም ያሏቸው አሉታዊ ተፅዕኖዎቻቻውም ከግምት ውሰጥ ሊገባ ይገባል፡፡ ለምሳሌ የአርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ ቴክኖሎጂ   በተራቀቀ መጠን በሰው ልጅ አቅም የሚሰሩ ስራዎች ልፋትና ድካምን ለማቃለል በሚል እሳቤ በዚሁ ቴክኖሎጂ ውጤቶች እየተተኩ በሚሄድበት ሂደት የስራ አጥነት ቁጥር አሁን ካለበት ከፍ የማለት እድሉ አጅግ የሰፋ ይሆናል፡፡

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የሀገሪቱን የቴክኖሎጂ መስክ ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር በሚያደርገው ጥረት  በሳይንስና ቴክሎጂው መስክ ለሀገሪቱ የላቀ አስተዋፅኦ ያበረክታል ተብሎ የታመነበትን “የኢትዮጵያ ባዮ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት” በማቋቋም የተለያዩ አመርቂ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል፡፡ ይህንን ዘርፍ የሚመራ አካል መቋቋሙ ደግሞ በአጭር ጊዜ የላቀ ለውጥ ለማምጣት ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል፡፡

    ሀገራችን መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገሮች ተርታ ለመሠለፍ የምታደርገውን  የልማት ግስጋሴ ማፍጠን የሚቻለው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ሁለገብ የላቀ ሚና አለው፡፡ በዚህ ዘርፍ በተጠናከረ መልኩ በመጓዝ ዉጤት ለማስመዝገብ የሚደረገውን ጥረት ለማቀላጠፍና የሚቋቋሙ ተቋማት ዉጤት ያለው ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ማስገኘት እንዲችሉ ለመስራት የባለ ድርሻ አካላት የላቀ ጥረት ወሳኝ በመሆኑ የሳይንሱን ዘርፍ እሩጫ በተደራጀ መልኩ መደገፍ ለስኬት የሚያደርስ ትልቅ ተግባር ነው፡፡

 

                             

 


 

   Click Here

61st GC Plenary 61st GC Plenary

H.E Dr Ing. Getahun Mekuria, Minister of Science and Technology of Ethiopia has addressed the 61st General Conference of IAEA at Vienna International Center, Vienna. The Minister said that Nuclear Technology is used in Ethiopia for peaceful purposes in Agriculture, Food Safety and Human Health sectors. He stressed the need for strengthened technical cooperation between the Agency and developing countries. He also condemned the weaponization of Nuclear energy and called for diplomatic solutions to resolve the current tensions in the Korean Peninsula.   

Video Video

The 3rd STI-WEEK News The 3rd STI-WEEK News

Weekly Visitor Status Weekly Visitor Status

// ]]>