Skip to Content

The 8th National S.T.I Award

The 3rd STI-WEEK Science Cafe Opening

The 3rd STI-WEEK Exhibition

IAEA Director General Yukiya Amano met with H.E.Dr.ING Getahun Mekuria

H.E. Dr. Ing. Getahun Mekuria, FDRE Minister of Science and Technology with Professor Afework Kassu, Deputy Minister.

His Excellency Dr./Eng. Getahun Mekuriya, Minister of Science & Technology, invited Mr Solomon Mulugeta to recognized him as an ambassador of science and technology.

Latest Video Latest Video

Latest News Latest News

Latest News


በሳይንስናቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የሴቶችና ወጣቶች ዳይሬክቶሬት ለዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የገንዘብ ድጋፍ አደረገ፡፡

18/01/2018
የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የሴቶችና ወጣቶች ዳይሬክቶሬት ከተለያዩ የመንግስት ተቋማትና የግል ድርጅቶች ፈንድ በማፈላለግ በአዳማና በአዲስ አበባ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲዎች በኢኮኖሚ እጥረት ምክንያት ትምህርታቸውን ለመከታተል የተቸገሩ 92 የኢንጂነሪግ ተማሪዎች በየሶስት ወር ለየአንዳንዳቸው 1200 ብር ድጋፍ እያደረገ ይገኛል፡፡

በሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የጥራት ስራ አመራር ስርዓት ደረጃ (ISO 9001:2015 ) ትግበራ ሰነድ እየተዘጋጀ ነው፡፡

18/01/2018
የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የጥራት ስራ አመራር ስርዓት ደረጃን (ISO 9001:2015) ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል ሰነድ የብሔራዊ የጥራት መሰረተ ልማት ዳይሬክቶሬት ከሪፎርም ዳይሬክቶሬት ጋር በመተባበር በሚኒስትር መስሪያ ቤቱ በተቋቋመው ግብረ ሀይል በቢሾፍቱ ከተማ ከጥር 05- 8/2010 ዓ.ም እየተዘጋጀ ይገኛል ፡፡

በጋምቤላ ክልል የሚገኘው የማጃንግ ደን በዮኔስኮ የከባቢ ህይወት ጥበቃ /የባዮስፌር ሪዘርቭ/ አለም አቀፍ ትስስር ውስጥ ገብቶ ተመረቀ

01/01/2018
በምረቃ ስነ– ስርዓቱ ላይ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂ. ጌታሁን መኩሪያ፣ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ሚኒስትሩ ዶክተር ነገሪ ሌንጮ፣ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር ዶክተር ጋትሉዋክ ቱት እንዲሁም የፌደራል እና የክልል የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

የሳይንስ ካፌ በአማራ ክልል ሊገነባ ነው፡፡

12/01/2018
የኢ.ፊ.ዲ.ሪ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከአማራ ክልል የሳይንስ ቴክኖሎጂና ኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ኮሚሽን ጋር በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በተመረጡ ዋና ዋና ከተሞች አምስት የሳይንስ ካፌዎችን ለመገንባት የሚያስችል የስምምነት ሰነድ ተፈራርሟል፡፡

የጊዜ ብክነትን እንደ ሃብት ብክነት የመመልከት ባህል ሊለመድ ይገባል፡፡

09/01/2018
የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር የሙያ ማህበራት እና የባለድራሻ አካላትን የ6 ወር እቅድ አፈፃፀም ገምግሟል፡፡

Message from the Minister Message from the Minister

Message from the Minister

H.E. Dr.-Ing. Getahun Mekuria Kuma has been appointed as the new Minister for Science and Technology beginning the 1st of November 2016. The appointment is part of Prime Minister Hailemariam Desalegn's cabinet reshuffle that came in the first week of November.

H.E. Dr.-Ing. Getahun has served the Ministry for the past two years as State Minister and Director General. Previously, H.E. Dr.-Ing. Getahun worked for the Addis Ababa Institute of Technology of Addis Ababa University in different academic and management capacities. He earned his BSc and MSc degrees in Electrical Engineering from Addis Ababa University. He completed his PhD degree in the same field at the University of Duisburg-Essen, Germany. The appointment of H.E. Dr.-Ing. Getahun as the Minister for Science and Technology is expected to galvanize the transformation process that the Ministry has already embarked on.

 

Back

የተሸላሚዎች ስራ

ግቢያ

የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የሳይንስና ቴክኖሎጂ የፈጠራ ስራዎችን በመደገፍ ጥቅም ላይ እንዲዉሉ የማድረግ እንዲሁም የሌሎች ሀገራት የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዉጤቶችን ወደ ሀገር ዉስጥ አስገብቶ የማላመድ ስራ ይሰራል፡፡ በአጠቃላይ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ እየተደረጉ ያሉ እንቅስቃሴዎች ላይ ባለድርሻ አካላትና የሚመለከታቸዉ ሁሉ አስተዋጽኦ ቢያደርጉ የሀገር ዕድገት ፈጣንና ቀጣይነት ያለዉ ይሆናል፡፡ በዚሁ መሰረት የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በ2010 ዓ.ም ለሽልማት ከበቁ ችግር ፈቺ የሆኑ የፈጠራ ስራዎችን ለማሳደግ እንዲያስችል ፈጠራዎቹን በእዉቀትና በገንዘብ የሚያግዙ አካላት ከፈጠራ ባለቤቶች ጋር በጋራ እንዲሰሩና እንዲሁም የተለያዩ ችግር ፈቺ የሆኑ ምርምሮች ወደ ህብረተሰቡ እንዲገቡ ብሎም ጥቅም ላይ እንዲውሉ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከነዚህ የምርምርና የፈጠራ  አካላት ጋር በጋራ መስራት የምትፈልጉ ወይም የምርምር/የፈጠራ ውጤቶቹ ተጠቃሚ መሆን የምትፈልጉ ከታች በተገለፁት አድራሻዎች በመጠቀም ማግኘት ትችሉ ዘንድ የፈጠራዎቹና የምርምሩ አጭር መግለጫ ከታች እንደሚከተለው ቀርቧል፡

የምርምሩ ርዕስ፡- የተሻሻለ የበቆሎ ዝርያ

ተቋምከባኮ ግብርና ምርምር ማዕከል

የምርምሩ አጭር መግለጫ

የሰብሉን ምርትና ምርታማነት አነስተኛ መሆን ከግምት ውስጥ በማስገባ የባኮ ብሔራዊ በቆሎ ምርምር ቡድን ከሌሎች ተባባሪ ማዕከላት ጋር በመሆን በርካታ የምርምር ሂደት እርከኖችን አልፎ ውጤታማ የሆኑ የተለያዩ የበቆሎ ዝርያዎችን እስከነሙሉ የአመራረት ዘዴና ሰብል ጥበቃ ቴክኖሎጂዎቻቸው ጋር ለተጠቃሚው ለቋል፡፡

ምርምሩ መነሻ ሀሳብ

የበቆሎ ሰብል በኢትዮጵያ ያለውን ሰፊ ጠቀሜታ መሰረት በማድረግ፤ በአገሪቱ ያለውን የሰብሉን ዝቅተኛ ምርትና ምርታማነትን ለማሻሻል፤ 1950 ጀምሮ ሲካ የቆየው የምርምር ሥራ የተለያዩ የተሻሻሉ የበቆሎ ቴክኖሎጂዎችን በማፍለቅና ለተጠቃሚዎች በማድረስ ጥረት ሲደረግ ቆይቷል፡፡ ሆኖም ከዘርፉ መገኘት የነበረበትን ምርት ማግኘት ባለመቻሉ ምክንያት ምርቱ አምራች አርሶ አደሩንም ሆነ እንደ ጥሬ ዕቃ የሚጠቀሙ አካላትን ተጠቃሚ ያደረገ አልነበረም፡፡

የምርምሩ ፋይዳ

የነዚህ የተሻሻሉ የበቆሎ ቴክሎጂዎች በምርምር መገኘትና ጥቅም ላይ መዋል ተከትሎ የበቆሎ ሰብል በአሁኑ ጊዜ በአገሪቱ አጠቃለይ ዓመታዊ ምርቱ 70 ሚሊዮን ኩንታል የደረሰ ሲሆን፤ ብሔራዊው አማካይ ምርታማነቱ ደግሞ 1990ዎቹ መጀመሪያ ላይ በሄክታር 12 ኩንታል ከነበረው ወደ 34.5 ኩንታል  አድጓል፡፡ ይህም በመቶኛ ሲሰላ፤ ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት የበቆሎን ምርታማነት 180% ያህል ለማሳደግ መቻሉን ያሳያል፡፡ ይህም አገሪቷ ቀደም ሲልጥሬ እቃነት የሚውል በቆሎን ከጎረቤት አገር ለማስገባት ታወጣ የነበረውን ከፍተኛ የውጪ ምንዛሬ አስቀርቷል፡፡ በዚህም በቆሎን በማምረት ላይ ያሉ አርሶ አደሮች ከሌላው መደበኛ ሰብሎች በተሻለ መልኩ በኑሮአቸው ላይ ከፍተኛ መሻሻል እንዲኖር አስችሏቸዋል፡፡

ተደራሽነት

·         በምርምሩ የተገኙ ቴክሎጂዎች ከሚመለከታቸው የመንግስትና የግል ማህበራት ጋር በመቀናጀት ተባዝተው ለአርሶ አደሩና ለከፊል አርሶ አደር እንዲሰራጭና ህብረተሰቡ እንዲጠቀምባቸው ተደርጓል፡፡

·         ማዕከሉ በየዓመቱ በአማካኝ እስከ 200 ኩንታል የተለያዩ አራቢና ቅድመ መስራች ዘሮችን እያባዛ ለኦሮሚያ፣ ለአማራ፣ ለጋምቤላ፣ ለደቡብ እና ለትግራይ ክልል ግብርና ምርምር ተቋማት ለአካባቢው ተስማሚ የሆኑ ዘሮችን አባዝቶ በማቅረብ ላይ ይገኛል፡፡

 

=======================================================================

የምርምሩ ርዕስ፡- ፔንታሚዲን የተባለን መድሀኒት በመጠቀም የሌሽማኒያን በሽታ ኤች አይ ቪ ባለባቸው ህሙማን ላይ እንዳያገረሽ መከላከል

ተቋምጎንደር ዮኒቨርሲቲ

የምርምሩ አጭር መግለጫ፡

የሌሽማኒያ በሽታ ኤች አይ ቪ ኤድስ በደማቸው በሚገኝ ሰዎች ላይ ተደርቦ ሲከሰት እስካሁን ድረስ ባሉን መድሀኒቶች አክሞ ሙሉ በሙሉ ማዳን አይቻልም፡፡ የሌሽማኒያ በሽታ ታክሞ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደገና በማገርሸት ጤንነትን በመጉዳት ሰዎችን ለሞት ይዳርጋል፡፡ በታከሙ በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ 60-70 በመቶ የሚሆኑት በሽታው በድጋሚ ያገረሽባቸዋል፡፡ የዚህ ምርምር አላማ ሌሽማኒያን ከታከሙ በኋላ እንዳያገረሽባቸው በመከላከል ህይወታቸውን ማዳን ነው፡፡

ፔንታሚዲን መድሀኒትን ለህሙማን በወር አንድ ጊዜ ለአንድ አመት በመስጠት እንዲሁም ለተጨማሪ አንድ አመት ደግሞ መድሁኒቱን እንዳይወስዱ በማድረግ ሙከራ ተደርጎ በተገኘው ውጤቱ በፊት ይታይ ከነበረው ከግማሽ በላይ ማገረሸቱን ቀንሶታል፡፡

የምርምሩ መነሻ ሀሳብ

በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜን ምዕራብ አካባቢ ከፍተኛ የሆነ የሌሽማኒያ በሽታ ስርጭት የሚታይ ሲሆን አብዛኝው የህመሙ ተጠቂዎች የኤች አይ ቪ ታማሚሆች ናቸው፡፡ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል በአካባቢው ህብረተሰብ ላይ የሚታዩ የጤና ችግሮችን በመለየት ምርምሮችን በማድረግ መፍትሄ ይፈልጋል፡፡ ይህ አንዱ በተደጋጋሚ የሚታይ ችግር በመሆኑ ትኩረት ተሰቶት ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር እንዲሰራበት ተደርጓል፡፡

የምርምሩ ፋይዳ

ይህ ምርምር በዚህ ህመም ተጎድተው መስራት፣ ማምረት እንዲሁም ቤተሰባቸውን መደገፍ ሳይችሉ የቀሩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ህይወት በመታደግ ጤናማና አምራች ዜጋ እንዲሆኑ ለማድረግ አስችሏል ፡፡

 

ተደራሽነት

·         የምርምሩ ዋና ዋና ግኝቶች አለም አቀፍ መጽሔት ላይ ታትመዋል፡፡

በብዙ አለም አቀፍና የሀገር ውስጥ የሳይንስ ጉባኤ መድረኮች ላይ ቀርቧል፡፡

==================================================================================

የፈጠራው ባለቤት ስም፡- አቶ ጌታቸው ገ/ህይወት

የፈጠራ ስራው ርዕስ፡- የአካል ጉዳተኞች መንከባከብያ ዊልቸር

  

የፈጠራ ስራው ውጤት፡- ይህ የአካል ጉዳተኞች ዊልቸር በውስጡ ሽንት ቤት፤ መታጠቢያ፤ መመገቢያ፤ የሽታ ማስወገጃ፤ ሴፕቲክ ታንክ/ ቆሻሻ ማጠራቀሚያ እንዲሁም በነፃነት እንዲጸዳዱ የሚያገለግል መጋረጃ ወዘተ… የተገጠሙለትና በቀላሉ ከቦታ ወደ ቦታ ለማንቀሳቀስ የሚያስችልና ቀላል ክብደት ያለው እንዲሁም ጠንካራ፣ ውበት የተላበሰና ከማንኛውም ዝገት ነፃ ሆኖ የተዘጋጀ ነው፡፡ አሁን በሰው ሀይል የሚንቀሳቀስ ቢሆንም ለወደፊት በሶላርና በኤሌክትሪክ ሀይል የሚንቀሳቀስ እንዲሆን ለማድረግ ታቅዷል፡፡

የፈጠራ ስራው ፋይዳ

*      የአካል ጉዳተኞችን እንቅስቃሴ በማገዝ በቀላሉ ከቦታ ወደ ቦታ እንዲጓጓዙ በማድረግ እንደማንኛውም ሰው ወደ ት/ቤት ፤ሀኪም ቤት እንዲመላለሱ ከማድረጉም ባሻገር የሚገጥማቸውን የስነ ልቦና ችግር በማቃለልና በማስወገድ በማንኛውም ማህበራዊ ጉዳዮች ተሳትፎ እንዲኖራቸው ያስችላል፡፡

*      አካል ጉዳተኞችና ህሙማን በሆስፒታል ሲተኙ ያለአስታማሚ ራሳቸውን መርዳት እንዲችሉ ማስቻሉ ፡፡ 

*      እናቶች በወሊድ ጊዜ ከፅዳት ጋር በተገናኘ ጉዳይ እንዳይቸገሩ ከፍተኛ እገዛ አድርጓል፡፡

*      በሆስፒታሎች ውስጥ የሚፈጠር የፅዳት ችግርን በማቃለል የሀኪሞችንና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞችን የሥራ ጫና ያቃልላል፡፡

*      ሃገራችን ዊልቼር ከውጭ በማስገባት የምታወጣውን ከፍተኛ ወጪ ማስቀረት ያስችላል፡፡

የፈጠራ ስራው ተደራሽነት

በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል፣ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል እና አቤት ሆስፒታል ውስጥ ገብተው አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡

የአእምሯዊ ንብረት ማስረጃ

የፈጠራው ባለቤት ይህ ፈጠራ በስፋት ተመርቶ ወደ ገበያ እንዲገባና ለአካል ጉዳተኞች እንዲሁም የማዋለድ አገልግሎት ለሚሰጡ ተቋማት በሰፊው እንዲዳረስና የህብረተሰቡን ችግር እንዲፈታ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ፈጠራውን በገንዘብ በመደገፍ በአጋርነት መስራት የምትፈልጉ እንዲሁም ፈጠራውን በእውቀት በመደገፍ ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ የምትፈልጉ አካለት በ0912 04 12 25 በመደወል የፈጠራ ባለቤቱን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

===============================================================================================

የፈጠራው ባለቤት ስም፡- አቶ ተወልደ ግርማይ ነጋ

የፈጠራ ስራው ርዕስ፡- የተዘጋ የመስኖ ግድብ መክፈቻ መሳርያ

የፈጠራ ስራው መነሻ ሃሳብ:- በትግራይ ክልል ዉሃ ሀብት ቢሮ 15 ኣመታት በፊት በሳርት ኮሚሽን ድርጅት ለመስኖና ለመጠጥ ዉሃ አገልግሎት ተብለዉ የተገነቡ ግድቦች በደለል ምክንት ተዘግተዉ ከአገልግሎት ዉጭ ሆነዉ መቆየታቸው፡፡ 

የፈጠራ ስራው ውጤት፡- የተለያዩ በደለል የተሞሉ ግድቦችን በማፅዳትና በመክፈት ግድቦች በጥቅም ላይ እንዲውሉ ያደርጋል፡፡

ያመጣው ፋይዳ:-

  •      ግድቦችን ይከፍታል፡፡ 

*      ግድቦች ለረጅም ጊዜ አገልግሎት እንዲሰጡ ያደርጋል፡፡

  •       እና ወጪ ይቀንሳል፡፡
  •      በመጠቀም በግብርና ላይ ምርታማነትን ይጨምራል፡፡

*      ግድቦች ከመደፈናቸው ጋር ተያይዞ የሚመጣን አላስፈላጊ ወጪ ያስቀራል፡፡

የፈጠራ ስራው ስርጭት/ተደራሽነት፡-  ይህ ፈጠራ የሀገር በቀል እውቀትንና ቴክኖሎጂን በመጠቀም መስራትና ጥቅም ላይ በማዋል መተግበር የሚቻል ነው፡፡ እስካሁን ባለው ሁኔታ ትናንሽና ቀላል ግድቦች ላይ ተግባራዊ ሆኖ ከ14 በላይ ግድቦች ተከፍተው ጥቅም ላይ ውለዋል፡፡

የአእምሯዊ ንብረት ማስረጃ

በተለያዩ ክልሎች ግድቦችን የምታስተዳድሩ አካላት የግድብ መዘጋት ችግር ካጋጠማችሁ ከፈጠራው ስራ ባለቤት ጋር በመገናኘት የዚህ ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ እንድትሆኑ እናስታውቃለን፡፡

አቶ ተወልደ ግርማይ    ስልክ ፡- 0914 76 30 09

===========================================================================================================

ተቋም፡- የደቡብ ግብርና ምርምር ኢኒስቲቲውት

የምርምሩ ርዕስ፡- የካሳቫ አመራረት፣ ምርት አያያዝና አጠቃቀም ቴክኖሎጂ

መግለጫ

ካሳቫ ከቁልቋል (Euphorbiaceae) ቤተሰብ የሚመደብ ሲሆን ከ200 በላይ ዝርያዎች አሉት፡፡ በዋናነት ለምግብነት የሚውለውም ከመሬት በታች የሚገኘው ኮረቱ/ስሩ ሲሆን በኃይል ሰጪነቱ ከስራስር ሰብሎች ሁሉ ተወዳዳሪ የለውም፡፡ ከሰው ምግብነት ባሻገር ለኢንዱስትሪ ጥሬ እቃነት ተፈላጊ ከመሆኑም ባሻገር
ለከብቶች መኖነት፣ ለዓሳ ልማት፣ ለዶሮ ምግብነት ለአፈር ልማት ይውላል፡፡ ወደ ኢትዮጵያ የገባበት
ትክክለኛ ዘመን ባይታወቅም ከ100 ዓመት በላይ እንዳስቆጠረ አንዳንድ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ካሳቫ
ከሌሎች ሰብሎች የሚለየው ሌላው ባህሪይ ለምነቱ በተሟጠጠ አፈር ላይ ተገቢ ምርት ከመስጠቱም
በተጨማሪ ድርቅን በመቋቋም በምግብ ራስን ለመቻል ለሚደረገው ጥረት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋል፡
፡ በዚህ ምክንያት የደቡብ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩትና የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት
በስራቸው ባሉ የተለያዩ የምርምር ማዕከላት አማካኝነት በተለያዩ ጊዜያት በተደረጉ የምርምር
እንቅስቃሴዎች አራት የተሻሻሉ የካሳቫ ዝርያዎች በሀገር አቀፍ ደረጃ እንዲለቀቁና ለአርሶ አደሩ እንዲዳረሱ
አድርጓል፡፡ ከዚህም ባሻገር ተያያዥነት ያላቸው ቴክኖሎጂዎች የአተካከልና የመስክ አያያዝ፣ አጠቃቀምና የድህረ-ምርት አያያዝ፣ የቴክኖሎጂ ብዜትና ስርጭት በሰፊው በሀገር አቀፍ ደረጃ እንዲካሄድ ተደርጓል፡፡

መነሻ ሀሳብ

እርጥበት አጠር በሆኑ አካባቢዎች፣ በተለይም በደቡብ ክልል ካሳቫ በተለምዶ የሚመረትና አርሶ አደሮች በእጃቸው ያሉትንና አነስተኛ ምርት በመስጠት የሚታወቁትንና ከተተከሉ እስከ ሶስት ዓመት ማሳ ላይ የሚቆዩ፣ የመርዛማነት መጠንናቸው ከፍተኛ የሆኑ ዝርያዎች ብቻ በተለምዶ እንደ ማንኛውም ስራስር ቀቅለው ከመጠቀም ውጭ ምንም የተሻሻለ ቴክኖሎጂ ተጠቀሚ አልነበሩም፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በተፈጥሮ የካሳቫ ምርት ቶሎ የመበላሸት ባህሪ ስላለው አርሶ-አደሩ ተጠቃሚ ሳይሆን ቆይቷል፡፡ ስለሆነም እነዚህን ችግሮች ለመቅረፍና አርሶ-አደሩን ተጠቃሚ ለማድረግ የተሻሻሉና ከፍተኛ ምርት የሚሰጡ ዝርያዎችን ማፍለቅ፤ የድህረ-ምርት አያያዝና አጠቃቀም ሁኔታን በማሻሻል አምራቹን ተጠቃሚ ለማድረግ ተብሎ የተካሄደ የምርምር ሂደት ያስገኘው ውጤት ነው፡፡


ውጤት

በተወሰነ ጊዜ ከአነስተኛ መሬት እጅግ በጣም ከፍተኛ ምርት ከመስጠቱም ባሻገር ከገንቢ ንጥረ ምግብ ይዘት ያለውና የተመጣጠነ የምግብ ይዘት ያለው ሰብል ነው፡፡ በምርምር የተለቀቁት ዝርያዎች 270-510 ኩንታል በሄክታር የሚሰጡ ሲሆን ከበቆሎ፣ ከስንዴ፣ ከጤፍ እና ሌሎች የመስክ እህሎች ጋር ሲነጻጸር 2-3 እጥፍ በላይ ምርት የሚሰጥ ሰብል ነው፡፡

 

ተደራሽነት

ካሳቫ በተለያዩ መንደገዶች መራባት ቢችልም ዋነኛውና ቀላሉ መንገድ ቆርጦ በመትከል ስለሆነ የምርምር ማዕከላትና ዘር አምራች ድርጅቶች በዓመት በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ቁርጥራጮችን ያመርታሉ፡፡ በተለያዩ መንግስታዊ ባልሆኑና መንግስታዊ በሆኑ ድርጅቶች አማካይነት ለአምራች አርሶ አደሮች ወቅቱን በጠበቀ ሁኔታ ጥራቱን ባሟላ መልኩ እየተዳራሰ ይገኛል፡፡ ለሽያጭ በሚቀርብበትም ጊዜ የአንድ ቁራጭ ዋጋ ከ0.40 ብር /አርባ ሳንቲም/ በታች ስለሆነ አርሶ አደሩ በቀላሉ በአነስተኛ ዋጋ ዘሩን አግኝቶ ማምረት ይችላል፡፡ ከካሳቫ ስር የተለያዩ ምግቦችን ለማዘጋጀት ታጥቦ፣ ተልጦ እና ተቆራርጦ በጸሐይ ላይ ተሰጥቶ እንዲደርቅ ይደረጋል፡፡ ይህ ሂደት በሚከናወንበት ጊዜ የምርምር ውጤት የሆኑ የካሳቫ መላጫዎች፣ መከታተፊያዎችና መሰነጣጠቂያ መሳሪያዎች በስራ ላይ እየዋሉ ይገኛሉ፡፡ እነኝህ መሳሪያዎች በተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች አማካይነት ካሳቫ አምራች ወደ ሆኑ አካባቢዎች በሰፊው ገብተው አርሶ አደሮችና በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ወጣቶች እየተገለገሉባቸው ይገኛሉ፡፡ እነኝህ የድህረምርት አያያዝ ላይ ከፍተኛ አስተዋጽዖ የሚያበረክቱ መሳሪያዎች በቀላሉ የሚባዙና ዋጋቸውም በጣም አነስተኛ ስለሆኑ በአሁኑ ሰዓት አርሶ አደሮች  በመግዛት እየተገለገሉ ይገኛሉ፡፡ በአጠቃላይ ቴክኖሎጂው በቀላሉ የሚባዛና ዋጋውም በጣም አነስተኛ ስለሆነ ለአነስተኛ አርሶአደሮች ተደራሽነቱ የሚያጠያይቅ አይደለም፡፡

ይንን የምርምር ውጤት በመጠቀም ምርትና ምርታማነታችሁን ለማሳደግ የምትፈልጉ በ0939 07 19 08 በመደወል መገናኘት ትችላላችሁ

 

 

 


 

   Click Here

61st GC Plenary 61st GC Plenary

H.E Dr Ing. Getahun Mekuria, Minister of Science and Technology of Ethiopia has addressed the 61st General Conference of IAEA at Vienna International Center, Vienna. The Minister said that Nuclear Technology is used in Ethiopia for peaceful purposes in Agriculture, Food Safety and Human Health sectors. He stressed the need for strengthened technical cooperation between the Agency and developing countries. He also condemned the weaponization of Nuclear energy and called for diplomatic solutions to resolve the current tensions in the Korean Peninsula.   

Video Video

The 3rd STI-WEEK News The 3rd STI-WEEK News

Weekly Visitor Status Weekly Visitor Status

// ]]>